ባለፋው ሳምንት ረቡዕ ነሐሴ 14 /2017 ዓ.ም ከኢቢሲ ኃላፊነት በተነሱት በአቶ ጌትነት ታደሰ ምትክ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የክትትል፣ ኢንስፔክሽንና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ቢኒያም ኤሮ መሾማቸውን ተወዳጅ ሚድያ አረጋግጧል።
አቶ ቢንያም ኤሮ፣ የማህበረሰብ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ በኢንሳ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገለገሉ ናቸው። በ 2013 ወደ ኢቢሲ በመግባት የሳይበር ክፍል ኃላፊ ሆነው የሠሩ ናቸው።
አቶ ቢንያም ኢንሳ አራት ዓመት ያገለገሉ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውንም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው ያጠናቀቁት።
አቶ ቢንያም ኤሮ ፓርላማው ሥራ ሲጀምር የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ቃለ መሀላ እንደሚፈጽሙ ይታወቃል።
(ተወዳጅ ሚድያ)
