አዲስ ቻምበር እና  የአሜሪካን ኤምባሲ በንግድ ማስፋፋት እና እድሎች ዙርያ ተወያዩ

Date:

በአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የተመራ የስራ አመራር አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ በመገኘት ከሚመለከታቸው ሀላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል ፡፡

ውይይታቸው በተለይም በአዲስ አበባና በተለያዩ የአሜሪካን ከተሞች  መካከል ያለውን የንግድ፣የገበያና የኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

የአዲስ ቻምበር አመራሮችን በአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዬን መሪ ግዌንዶሊን ግሪን እና በኤምባሲው የንግድ ጉዳዮች ሀላፊ ሚስተር ሊዬን ስካርኒሺስኪ ከሌሎች የሚመለከታቸው ሀላፊዎች ጋር በመሆን ተቀብለው አነጋግረዋል ።

ሁለቱ ተቋማት (አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ) በቀጣይ የንግዱ ሕብረተሰብን እርስ በእርስ ለማገናኘት፣የንግድ እድሎችና መረጃዎች በመለዋወጥ፣ የንግድ ለንግድ ግንኙነት  የሚፈጠርበት ሁኔታ በአጠቃለይ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በኢትዮጵያና በአሜሪካን መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እያደገ የመጣ ሲሆን በተለይም አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ለረጅም አመታት ካላቸው አጋርነት አኳያ ለንግዱ ማደግ ሚናቸው ጉልህ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

አዲስ ቻምበር ከዚህ በፊት በአሜሪካን የተለያዩ ከተሞች ከሚገኙ ንግድ ምክር ቤቶች ጋር የነበረውን ግንኙነት በይበልጥ በማጠናከር ንግድና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ከኤምባሲው ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ተገልጿል ።

የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ መጠን እ.ኤ.አ በ2024 ከ 1ቢሊየን ዶላር በላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...