አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ቀንን ወሰነ

Date:

ተማሪዎቹንም ሰኔ 21 እንደሚያስመርቅ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ ስም ይፋ ተደርጎ የተሰራጨውን የአካዳሚክ ካላንደር ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር ማረጋገጥ ችሏል። አንድ የተቋሙ አመራር ” ከመጨረሻው ሐምሌ 2 ከሚለው ውጪ ሁሉም ትክክል ነው። የመጨረሻው ሐምሌ 8 ነው የሚሆነው ” ብለዋል።

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ይፋ ባደረገው ካላንደር የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ቢጠቁምም ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ስለ ፈተናው ቀን በይፋ ያሳወቀው ቀን የለም።

በሌላ በኩል የመውጫ ፈተና በድጋሜ የሚፈተኑ ተፈታኞች  በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ ” አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገምን እንገኛለን ” ሲል ገልጿል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱም አመልክቷል።

ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

እስካሁን ድረስ ምዝገባ ያልፈጸሙ ተማሪዎች የመመዝገቢያው አድራሻ / ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በአግባቡ እየሰራላቸው እንዳልሆነ በጠቆም የምዝገባ ጊዜው እንዲራዘም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ገምግሞ ይፋ የሚያደርገው አዲስ ነገር ካለ የምንከታተለው ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪ ደሞ ” በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታቸው ተሰርዟል ” የተባሉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ አለባቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...