ኢሎን መስክ አዲስ የበይነ መረብ ኢንሳይክሎፒዲያ ይፋ አደረገ

Date:

ቢሊየነሩ ኤሎን መስክ፣ ግሮኪፒዲያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ለዊኪፒዲያ አማራጭ እንደሚሆን ገልጿል።

መስክ ባለፈው ወር ዊኪፒዲያ ለፅሁፎቹ እነ ኒውዮርክ ታይምስን በምንጭነት እንደሚጠቀም አንስቶ የሚሰጠው መረጃ የተዛባ ነው በማለት አዲስ ኢንሳይክሎፒዲያ እንደሚያወጣ አስታውቆ ነበር።

ግሮኪፒዲያ ላይ እንደ ዊኪፒዲያ ሰዎች መፃፍና ማስተካከል የማይችሉ ሲሆን፤ ፅሁፎቹ ግሮክ በተሰኘው የራሱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሃቅ ማጣራት ይደረግባቸዋል ተብሏል። ሰዎች ምንም እንኳን ፅሁፎቹ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ባይችሉም የተሳሳተ ነው ብለው የሚያምኑት መረጃ ካለ እንዲስተካከል ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

ዊኪፒዲያን የሚያስተዳድረው ዊኪሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ግሮኪፒዲያ እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት እየጣረ መሆኑን ገልፆ፣ የዊኪፒዲያ እውቀት ሁሌም የሰው ነው፤ ግሮኪፒዲያ ራሱ ለመኖር ዊኪፒዲያ ያስፈልጋል”ብሏል።

ዊኪፒዲያ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝኛ የተፃፉ ከ7.1 ሚሊየን በላይ ፅሁፎች ሲኖሩት፣ ግሮኪፒዲያ አሁን ላይ ከ885 ሺህ በላይ ፅሁፎች አሉት።

ኤሎን መስክ በተጨማሪ በዚህ አመት መጨረሻ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያው ግሮክ፣ ዊኪፒዲያን በምንጭነት እንዳይጠቀም እንደሚደረግ ገልጿል ሲል ቲክቫህ መጋዚን አስነብቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...