በፋርስ ባሕረ ሰላጤ፣ በኦማን ባሕር ወይም በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ሁኔታዎችን ይበልጥ የሚያወሳስብ ማንኛውም ዓይነት ዕርምጃ ጥበብ የጎደለው መሆኑንና ማንኛውም ኃላፊነት የሚሰማው ወይም ምክንያታዊ የሆነ አካል እንዲህ ዓይነቱን አደገኛ ዕርምጃ አይወስድም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ዋና ዋና መግለጫዎች፦
🟠 የኔቶ እና የአውሮፓ ኅብረት አገራት እውነትም ኃላፊነታቸውን መወጣት የሚፈልጉ ከሆነ፤ ለቀውሱ ዋነኛ መንስኤ የሆኑትን አሜሪካንና እስራኤልን ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው።
🟠 የአሜሪካ እና የእስራኤል ወታደራዊ ትንኮሳ ከመከሰቱ በፊት፣ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል መደበኛ የባሕር ላይ ትራፊክ በሰላም ይንቀሳቀስ ነበር።
🟠 ኢራን፣ የባሕር ዳርቻ አገር እንደመሆኗ መጠን፣ ደኅንነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ዕርምጃዎችን ለመውሰድ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሙሉ መብት አላት።
🟠 መርከቦች አስተማማኝ ጉዞን ለማረጋገጥ ከኢራን ጦር ኃይል ጋር ቅንጅት በመፍጠር በሰርጡ በኩል መጓዛቸውን ቀጥለዋል።
🟠 ዋሽንግተን በቅርቡ በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ላይ ያደረገችው ሕገ-ወጥ ጣልቃገብነት ሁኔታውን ይበልጥ አባብሶታል።
