ኢትዮ ቴሌኮም ከጅቡቲ እና ሱዳን የቴሌኮም ኩባንያዎች ጋር ለመስራት ተስማማ

Date:

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የሦስትዮሽ ስምምነቱ የጋራ የዲጂታል ወደፊት ዕጣ ፈንታችንን ለመገንባት የሚያስችል ነው።

የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ ጠንካራና ከፍተኛ አቅም ያለው እንዲሁም አፍሪካን በዲጂታል የሚያስተሳስር የኮኔክቲቪቲ ኮሪደር ለመፍጠር የተወሰደ ወሳኝ ርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይም የጅቡቲን የባሕር ውስጥ የፋይበር ኬብሎች በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ከሱዳን ጋር በማስተሳሰር ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን የሚያጠናክር፣ አስተማማኝ የየብስ መስመር ተግባራዊ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

የጅቡቲ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ አሶዌ ቡህ በበኩላቸው÷ የሆራይዘን ፕሮጀክት ለሀገራቱ የጋራ እድገትና ብልጽግና ያለንን ራዕይ መሰረት በማድረግ በቀጣናው የቴሌኮም መሠረተ ልማትና ትስስር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ፕሮጀክት ከመሠረተ ልማት ግንባታነት ባሻገር በአፍሪካ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መካከል ለሚደረግ የፈጠራ አጋርነት ህያው ምስክር ነው ያሉት ደግሞ የሱዳቴል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማግዲ ሞሀመድ ናቸው።

የተፈረመው ስምምነት ከፍተኛ አቅም ያለው ድንበር ተሻጋሪ የኦፕቲካል ፋይበር መሠረተ ልማት ለመዘርጋት እና የቀጣናውን ዲጂታል ትስስር ወደ ላቀና አስተማማኝ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...