ኢትዮጵያ የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራን በ334 ወረዳዎች አስፋፋች

Date:

የኢትዮጵያ የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን የሚኒስትሮች ስቲሪንግ ኮሚቴ የስድት ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፕሮግራሙን ተደራሽ ለማድረግ የመንግሥትና የአጋሮችን ድጋፍ በማስተባበር እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ በሰቆጣ ቃልኪዳን የስድት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ የጤና ሚኒስቴር በማህበራዊ የትሥሥር ገፁ አስነብቧል።

በ2007 ዓ.ም የተፈረመው የሰቆጣ ቃልኪዳን ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመከላከል ወጥኖ የተነሳ ነው። ቃልኪዳኑ ከ7.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕጻናትን በ15 ዓመት ውስጥ ከመቀንጨር ለመታደግ ያቀደ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...