• ማይክሮሶፍትና አፕል ይከተላሉ
ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቺፖችንና ሱፐር ኮምፒውተሮችን በማምረት የሚታወቀው ኢንቪዲያ ኩባንያ የአክሲዮን ዋጋ 2.4 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡
ኩባንያው በዓለማቀፍ ደረጃ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን መሠረት ያደረገ የቴክኖሎጂ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ በዘርፉ መሪነቱን እንዲይዝ አስችሎታል፡፡
ኢንቪዲያ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ2023 አንድ ትሪሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡
ኩባንያው በሁለት ዓመታት ውስጥ በፍጥነት በማደግ አሁን ላይ 4 ትሪሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ ላይ በመድረስ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሆኑን ቢ.ቢ.ሲ ዘግቧል፡፡
ኢንቪዲያን ተከትለዉ ማይክሮሶፍት በ3.8 ትሪሊዮን ዶላር እንዲሁም አፕል በ3.1 ትሪሊዮን ዶላር የገበያ ድርሻ ላይ እንደሚገኙም መረጃዉ ጠቁሟል።
