በሄኖክ በቀለ ተደርሶ የተዘጋጀው “እውነት እና ፍቅር” የተሰኘው መንፈሳዊ ተውኔት የፊታችን ሰኔ 29 2017 ዓ.ም በቫምዳስ ሲኒማ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።
መንፈሳዊ ተውኔት የኃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል።
ተውኔቱ ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ ጭብጥ ቢኖረውም ማንም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ መቅረቡንም አዘጋጆቹ ለኢቨንት አዲስ ሚዲያ መረጃውን ተገልጿል።
የ55 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ይህ ተውኔት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የንግድ ተውኔት መሆኑንም ሰምተናል።
