📣የአርሰናል ደጋፊዎች ጥምረት ፒኤስጂ ላይ ቅሬታውን ሊያቀርብ ነው ። በመልሱ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ 2000 ደጋፊዎች ብቻ የተፈቀደላቸው አርሰናሎች ይህ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ካወጣው ህግ የሚፃረር ነው ባይ ናቸው ። ከሜዳ ውጭ የሚጫወት ቡድን 5% ቢፈቀድለትም በ500 አንሶብናል ባይ ናቸው ። የፈረንሳይ ፖሊስ ከፀጥታ ስራ ጋር በተገናኘ ከአምና የሊቨርፑል ጨዋታ ጀምሮ አስቶን ቪላን አካቶ 4.1% ብቻ እንዲሆን የሚል ትዕዛዝ መስጠቱ ተነግሯል ።
🎒 አርሰናል ከባርሴሎና ለፍፃሜ ደርሰዋል ።
የአርሰናል ሴቶች ቡድን ለአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መብቃቱን አረጋግጧል ። ከ18 አመት በኋላ እንስቶቹ መድፈኞች የፈረንሳዩን ሊዮን 4ለ1 ከሜዳቸው ውጭ አሸንፈው ለፍፃሜ በቅተዋል ። በፍፃሜው ቸልሲን በደርሶ መልስ 8ለ1 ካሸነፈው ባርሴሎና ጋር በሊዝበን ይፋለማሉ ።
🛑 አርሰናል እና ቡካዮ ሳካ ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል ። የተጨዋቾች የስምምነት አመት መጨረሻ ሲደርስ የተጨዋቾችን ልብ ማሸፈት ለለመደው ሪያል ማድሪድ ተስፋ አስቆራጭ ነው
🔴 የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋቾች ጃክ ዊልሼር እና አሮን ራምሴ በአሰልጣኝነት በተቃራኒ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ ይገናኛሉ ። ጃክ ዊልሻየር የሚያሰለጥነው ኖርዊች ሲቲ መውረዱን ያረጋገጠውን ካርዲፍ ሲቲን በሜዳው ያስተናግዳል ።
🔴 አጥቂ ፍለጋ ወደ ገበያ የሚወጣው አርሰናል የሊያም ዴላፕ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል ። ዋጋው 30 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ መሆኑ የበርካቶችን ትኩረት ስቧል ።
ሁሉ አዲስ ሬድዮ
