“ከጦር ይልቅ ዲፕሎማሲ ሰርጡን ይከፍታል “ህንድ

Date:


ህንድ “የሆርሙዝ ሰርጥን ዳግም ለመክፈት ዲፕሎማሲ ቁልፍ ጉዳይ ነው “አለች።

ኒው ደልሂ ከወታደራዊ አካሄድ ይልቅ ዲፕሎማሲን መከተል ከኢራን ጋር ያለውን ልዩነት እንደሚፈታ አሳስባለች።

በሆርሙዝ ሰርጥ መርከቦችን እንደወትሮው ለማንቀሳቀስ ከቴህራን ጋር መወያየት ወሳኝነት ያለው ጉዳይ ነው ተብሏል።

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኒው ደልሂና በቴህራን መካከል በተደረገ ድርድር ሁለት የህንድ ባንዲራን የያዙ  መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸዋል የሚለውን በማሳያነት አንስተዋል።

በሌላ በኩል የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዚሁ ሰርጥ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ዳውኒንግ ስትሪት መሪዎቹ የሆርሙዝ መከፈትን አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተው መምከራቸንም አሳውቋል።

ስታርመር ከካናዳው አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ ጋርም በቀጠናው ቀውስ እና በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ   መወያየታቸው ተሰምቷል።

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺም “ለድርድር ዝግጁ አይደለንም
፣ለረዥም ጦርነት ቴህራን ተዘጋጅታለች” ማለታቸው የሁኔታውን መወሳሰብ ጠቋሚ ያደርገዋል።

ዘገባው የአልጀዚራና ዋሽንግተን ፖስት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...