የአበበች ጎበናን ህይወት የሚተርክ ፊልም ተመረቀ

Date:

የአበበች አደራ” በሚል ስያሜ እንዲሁም “ፍቅር፣ ርህራሄ፤ ወደር የማይገኝለት ሰብዓዊነት!”በተሰኘ መሪ ቃል ህይወት የሚተርክ ፊልም ምርቃት እና ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር  በትናትናዉ  እለት ተካሄዷል።

መርሐ ግብሩ ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የሚታወሱባቸውንና ትውልድ ሊያውቀውና ሊማርበት የሚገባ የህይወታቸው እሴቶችና መርሆዎችን ለማስገንዘብ እንዲሁም ለትውልድና ለኢትዮጵያ መንግስት አደራ ሰጥተው የሄዱትን ድርጅት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

የክብር ዶክተር አበበች ጎበና የአበበች ጎበና ቻሪቲ መስራችና ባለራዕይ ሲሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን በማሳደግና በአያሌ የሰብዓዊነት ተግባራቸው በመላው ዓለም እውቅናን ያገኙ ሰው ናቸው፡፡

በ1972 ዓ.ም ወላጆቻቸው በረሀብ የሞቱባቸው ሁለት ህፃናትን በማንሳት የተጀመረው ጉዞ ከአርባ ሰባት ዓመታት በኋላ እንኳ ብዙዎች የሚጓዙበት የርህራሄና የሰብዓዊነት ጎዳና ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ከአመታት በፊት በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው እኒህ ታላቅ እናት በስራ ወዳድነታቸው፤ በደግነታቸውና በሰብዓዊ ተግባራቸው በትውልዶች ይታወሳሉ፡፡ ስራቸውም በአያሌ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ህያውነት ውስጥ ተጠብቆ ይኖራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...