ከፍተኛ መኮንኑ ፣ መሐንዲሱ ፣ ደራሲው ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው አረፉ!

Date:

የአባታቸውን ብ/ጀ ጌታቸው ናደው የውትድርና ፈለግ በመከተል የውትድርና ህይወትን መረጡ። የቀኃሥ ገነት ጦር ት/ቤት ምሩቅ መኮንን በመሆን የውትድርና ህይወት ሀ ብለው ጀመሩ። የአባታቸው በደርግ በግፍ መገደል ተከትሎ ለ7 አመታት በእስር አሳልፈዋል።

በመቀጠል የቀለም ትምህርት በመግፋት በሲቪል ምህንድስና ተመርቀዋል። በስራቸውም በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እና ኤርፖርቶች ላይ አሻራቸውን አኑረዋል።

ከመንግስት ለውጥ በኋላም በዚሁ የሲቪል ምህንድስና ሞያቸው ለረጅም አመት ሠርተዋል። በጡረታ ዘመናቸው እና የመኪና አደጋ ከደረሰባቸው በኋላም 3 መፅሀፍትን ፅፈው ለተደራሲያን አቅርበዋል።

ከጋዜጠኛ ደረጀ ሐይሌ ጋር ATRS TV “በነገራችን ላይ ” በሚል ፕሮግራም በ3 ክፍሎች ተቀንብቦ በቀረበው ቆይታቸው ብዙ መሣጭ ታሪኮችን አጫውተውን ነበር። የተዋቂው ሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ አባት ናቸው።የጀነራሉ ልጅ ፣ ወታደሩ ፣ መሐንዲሱ ፣ ፀኃፊው ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ነፍስን ፈጣሪ ይማር።

ለቤተሰብ ፣ ወዳጅ እና ዘመድ እንዲሁም ለባልደረቦቻቸው መፅናናትን ያድል።

Via: አብዮታዊው ሰራዊት ገፅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...