በእስራኤል ቴላቭ ራማት ጋን በኬንያ ኢምባሲ አቅራቢ የደረሰ ፍንዳታን ተከትሎ የኬንያ መንግስት ኢምባሲዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቀረበ፡፡
ሁለቱም ወገኖች ጦርነት ማቆም አለባቸውም ሲልም አስጠንቅቋል፡፡
የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤት ዋና ጸሀፊ ኮሪ ሲንግ ኦይ በውጭ ዲፕሎማቶች ላይ የሚደረግ የትኛውም ጥቃት ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ ስለሆነ መወገዝ ያለበት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ተቋማቱ ከማንኛውም ግጭት መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኮሪ ሲንግ ኦይ በእስራኤል የኬንያ አምባሳደርን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን አሁን ላይ የኢምባሲው ሰራተኞች ከቤታቸው ሆነው ስራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ እና በሰላም እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
