የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳኦ ቶሜ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ 1ለ0 አሸንፏል።
ለዋልያዎቹ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ቸርነት ጉግሣ ማስቆጠር ችሏል።
ኢትዮጵያ የቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታውን በድምር ውጤት 4ለ0 በማሸነፍ ምድብ ድልድሉን ተቀላቅላለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚያደርግ ይሆናል።
የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ድልድል በቅርብ ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።
