ሰሜን ኮሪያ በሀገር ውስጥ የምትጠቀምበትና ከተለመደው የዓለም ካርታ የተለየ መልክ ያለው ካርታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ተከትሎ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
ይህ ካርታ የፓስፊክ ውቅያኖስን መሃል ላይ ያደረገ ሲሆን የኮሪያ ልሳነ ምድርን በጉልህ በማሳየት ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያን እንደ አንድ ሀገር አድርጎ ስሎ አቅርቧቸዋል።
በሬዲት (Reddit) ማህበራዊ ገጽ ላይ መረጃውን የተመለከቱ ተጠቃሚዎች እንደገለጹት በካርታው ላይ የጃፓን መገኛ ቦታ ተቀይሮ የሚታይ ሲሆን የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ የተወሰኑ ክፍሎች ደግሞ ጨርሶ የማይታዩ ወይም እጅግ አነስተኛ ሆነው ተስለዋል።
ካርታው አገራት የምዕራባውያንን የካርታ አሰራር ልምድ ከመከተል ይልቅ ራሳቸውን ማዕከል አድርገው ዓለምን እንዴት እንደሚመለከቱ የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።
ምንም እንኳን ይህ ካርታ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ወይም በሕዝባዊ ቦታዎች ላይ በቋሚነት ጥቅም ላይ ስለመዋሉ ከመንግሥት ወገን የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ ባይኖርም በዲጂታል መድረኮች ላይ ግን ሰፊ ክርክር ቀስቅሷል።
ካርታው ሰሜን ኮሪያ ያላትን የፖለቲካ አቋም እና ዓለምን የምታይበትን መንገድ የሚያንፀባርቅ እንደሆነም ታዛቢዎች ይናገራሉ።
