የመኪና ማቆሚያን ለሌላ አገልግሎት ሲጠቀሙ የተገኙ ህንፃዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ ከሚፈጥሩ ምክንያቶች አንዱ በተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት የሚሄዱ ተገልጋዮች ተሸከርካሪያቸውን ከዋና መንገድ ዳር ስለሚያቆሙ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የፓርኪንግ እና የመንገድ ትራፊክ መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጌታቸው ለኤፍኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የትራፊክ መጨናነቅን ለማቃለል ባለፈው ዓመት የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 165/2016 ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግም በ11ዱ ክፍለ ከተሞች የህንፃ ስር የመኪና ማቆሚያን ለተለያዩ አገልግሎት ሲጠቀሙ የነበሩ 1 ሽህ 286 ህንፃዎችን በመለየት ስፍራውን ለተፈቀደለት አላማ እንዲያውሉ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በመንገድ ዳር የሚገኙ በጥናት የተለዩ 1ሽህ 227 ህንፃዎች ስር ያሉ  የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን  በመለየት መንገድ ላይ ይቆሙና ከተማውን ያጨናንቁ የነበሩ ከ21 ሺህ 6 መቶ በላይ ተሽከርካሪዎች  እንዲቆሙበተ ማድረግ ተችሏል ብለዋል አቶ ቢኒያም፡፡

የህንፃ ስር የተሸከርካሪ ማቆሚያውን አሁንም ለፑል ቤት፣ ለስቶር፣ ለጭፈራ ቤት፣ ለጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ለሌላ አገልግሎት እየተጠቀሙ ያሉ 55 የህንፃ ባለቤቶች መቀጣታቸውንና ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...