የሥላሴን አኗኗር በስጋዊ ስሌት የማንመረምረውም መንፈሳዊ በመሆኑ ነው

Date:

የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት ስንማር ከሂሳብ ቀመር ሕግ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ያሻል። ምክንያቱም መንፈሳዊዉ ጥበብ ሥጋዊዉን ጥበብ ወይም ፍልስፍና ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀትና ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና የሃይማኖት ነገር ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊና በሃይማኖት ሆኖ በመንፈሳዊነት የሚታወቅና የሚታመን ነው።

ሥላሴ፣ ሠለሰ ሶስት አደረገ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፤ ሥላሴ ማለት ሶስትነት ማለት ነው። በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን፣ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ከዓለም በፊት የነበረ ነው እንጂ ኋላ የተገኘ አይደለም፡፡

ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ የሥላሴ አንድነት በባህርይ፣ በህልውና፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ በመፍጠር በመሳሰሉት ነው፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም የአንድነትና የሦስትነት ስም ነውና በስም፣ በግብርና በአካል ሦስት እንላለን፡፡ የሰው ነፍስ የቅድስት ሥላሴ ምሳሌ ናት፡፡

ይኸውም አብ በልብ፣ ወልድ በቃል፣ መንፈስ ቅዱስ በእስትፋስ ይመሰላሉ፡፡ በእግዚአብሔርነቱ፤ ልብ፣ ቃልና ሕይወት አለ። ነፍስ ሶስት ባህርያት ቢኖሯትም አንድ እንደምትባል እግዚአብሔርም ሶስት ስም፤ ሶስት ግብር፤ ሶስት አካል፤ ቢኖረውም አንድ አምላክ እንጅ ሶስት አማልክት አይባልም፡፡

ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈሰ ቅዱስ ለየራሳቸው ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል፣ አላቸው። የፍጡራን አካል የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚመጠን፤ የሚወሰን፣ ሲሆን የሥላሴ አካል ግን፤ የማይታይ፣ በእጅ የማይዳሰስ፣ በቦታ የማይወሰን፣ በሁሉም ምሉዕ ነው። የቅድስት ሥላሴ ምሕረትና ቸርነት አይለየን፡፡

ገዳማውያኑ ዓለምን ትተው ሲመንኑ ይህን ምሕረትና ቸርነት ተስፋ አድርገው ስጋዊውን ክብር ንቀው ነው፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡ 

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...