የሰብዓዊ አቅርቦት እንዳላዳርስ የመንገድ መዘጋት እንቅፋት ሆኖብኛል

Date:

በአማራ ክልል ባለው የጸጥታና የሰላም እጦት ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀስ መቸገሩን የአማራ ክልል የሲቪል ማኅበረሰብ ሕብረት አስታውቋል።

በግጭቱ ሳቢያ በርካታ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ በመሆኑ፣ የእርዳታ አቅርቦቶችን በተገቢው መንገድ ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኗል ሲልም ሕብረቱ ገልጿል።

የክልሉ ሲቪል ማኅበረሰብ ሕብረት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ደስታ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሔደ ባለው ግጭት ምክንያት በተለይ የሕጻናት የመማር መብት፣ የዜጎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ እና ተገቢውን የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እየተጣሰ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም፤ ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት፤ ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች ለደህንነታቸው በመስጋት በየብስ ትራንስፖርት ተንቀሳቅሰው ከመስራት ይልቅ የአውሮፕላን ጉዞ መምረጣቸው የሰብአዊ ድጋፍ የማድረግ ሥራቸው ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

በአማራ ክልል ያለው የሰላም እጦት ማኅበረሰቡን ለማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ለተለያዩ ችግሮች እየዳረገ በመሆኑ፤ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም የሕብረቱ ዋና ዳይሬክተር አሳስበዋል።

በዚህም መንግሥት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በመነጋገር ወደ ምክክር እና ድርድር እንዲመጡ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

በተለይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲከበርና በሰላም ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...