አሁን ላይ የተቋሙን አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ደንበኞች የሚፈልጉትን ውል የሚያጽፉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አካባቢ የጽሁፍ አገልግሎት በሚሰጡ ግለሰቦች አማካኝነት ነው።ይህም ተገልጋዮችን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርጋቸው እንደሆነ ተቋሙ አሳውቋል።
በስምምነቱ ላይ ኢትዮ ፖስታ ቅርንጫፉን ወደ ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ በማስፋት የጽሁፍ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን እወቁልኝ ብሏል።
በግለሰቦች እየተሰጠ ያለው የፅሁፍ አገልግሎት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ እንደነበር አየተነገረ ነው።
