የቱርኩ ፕሬዚዳንት  ወደ  ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ ተራዝሟል ?

Date:

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመሩ ተገልጾ ነበር።

በወጡት ሪፖርቶች ፕረዚደንቱ  ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ መሐመድ ቢንዛይድ የጤና ሁኔታ ጋር ተያይዞ ተራዝሟል። ሁለቱ የሀገር መሪዎች በስልክ ውይይት ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው።

ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞስ ?

የቱርክ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ፕረዚዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ እንደተጠበቀ ነው ሲል አስታውቋል።

ፕረዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ግብዣ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዙ የገለጹት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ቡርሃኔትን ዱራን ውይይቶቹ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እንዲሁም በክልላዊ እድገቶች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ድርድር የተጠናቀቀባቸው እንደ ንግድ፣ የመከላከያ የተለያዩ  መሠረተ ልማቶች ላይ ስምምነቶች እና ሰነዶች እንደሚፈረሙ ይጠበቃል ሲሉም አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...