የቲ-ካስቲንግ ኤጀንሲ ዌብሳይትና አፕሊኬሽን ስራ ጀመረ

Date:

የትወናና የሞዴሊንግ ምልመላ ወኪል(ካስቲንግ ኤጀንት) የሚያስተዋውቅ እንዲሁም የተደበቀን ተሰጥኦን ገሀድ ለማዉጣት የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው የተነገረለት ቲ ካስቲንግ ኤጀንሲ ዌብሳይትናና አፕሊኬሽን በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡

በሀገራችን እንዲሁም  በዉጭ ሀገራትና ከተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ስራዎች ጋር በትብብር በመስራት በሚታወቀው “ቴዲ ሾዉ መልቲ ሚዲያ” አማካኝነት በከፍተኛ ጥናት የበለፀገዉ ዌብሳይትና አፕሊኬሽን፣ “ቲ_ካስቲንግ ኤጀንሲ!” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን  በሀገራችንም የመጀመሪያው የዲጂታል የታለንትና ተሰጥኦ ምልመላ ወኪል  እንደሆነም ተነግሯል።

የቲ-ካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊዎች እንዳብራሩት፤”በአገራችን ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ታላላቅ ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች መተወን ለሚፈልጉ፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ስራ፣ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች፣ የሲኒማ ፊልሞች ፣ የሙዚቃ ክሊፖች ላይ የትወና ስራ ያመቻቻል፡፡

እንዲሁም ብራንድ አምባሳደርነት ሙያን ከፈላጊ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት ምቹና ቀጥታ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ዘመናዊ የዲጂታል ፕላትፎርም ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...