የትራምፕ ከ1,000 በላይ የአሜሪካ ሰራተኞችን ከስራ አሰናበቱ

Date:

የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል የመንግስት ሰራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚያደርገው ጥረት፣ ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ የሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።

ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ባለፈው አርብ ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተላከ እና በቢቢሲ የአሜሪካ ዜና አጋር በተገኘ ማስታወቂያ መሰረት፣ በግዳጅ ከስራ ከተሰናበቱት ውስጥ 1,107 የሲቪል ሰርቪስ እና 246 የውጭ አገልግሎት ሰራተኞች ይገኙበታል ተብሏል።

ከዚህ ቀደምም፣ የፌደራል መንግስትን በስፋት የማደራጀት ጥረት አካል በመሆን፣ ከ1,500 በላይ የሚሆኑ ሌሎች የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በፈቃደኝነት ስራቸውን ለቀው እንደነበር ተገልጿል።

ይህን የጅምላ ሰራተኛ ቅነሳ የሚተቹ ወገኖች፣ ቅነሳው የመስሪያ ቤቱን ስራ በእጅጉ እንደሚጎዳ ሲከራከሩ ቆይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...