የትራምፕ የታሪፍ ውሳኔ አሜሪካውያን ሸማቾችን የሚጎዳ ነው ተባለ

Date:

ዶናልድ ትራምፕ፣ በውጭ ንግድ ላይ የጣሉት ቀረጥ የዓለም የንግድ ስርዓትን የሚያዛባ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ተናገሩ፡፡ የትራምፕ የታሪፍ ውሳኔ አሜሪካውያን ሸማቾችን የሚጎዳ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ እንደገለጹት፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ጋር በሚነግዱ የዓለም ሀገራት ላይ በሙሉ ከ10 በመቶ ጀምሮ የጣሉት ቀረጥ የዓለምን የንግድ ስርዓት የሚያዛባ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ ቀረጥ የተጣለባቸው ሀገራትም፣ የራሳቸውን ኢኮኖሚ ለመከላከል በአሜሪካ ላይ ቀረጥ እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

የዓለም ሀገራት ለትራምፕ ውሳኔ የሚሰጡት ምላሽ መልሶ የሚጎዳው አሜሪካንን ነው ያሉት ምሁሩ፤ ይህ አይነቱ ሁኔታ የዓለምን የንግድ ሥርዓት እንደሚያዛባም አስታውቀዋል፡፡ የአሜሪካ ትልቁ አቅም ከሌሎች ጋር መነገድና ራሷን መቻሏ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ላይ ግን እንደ ቻይና ያሉት ሀገራት ብሪክስን ይዘው በራሳቸው ገንዘብ ለመነገድ እየወሰኑ ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚጎዳው አሜሪካንን ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

አሜሪካ የአረቢካ ቡናን ጨምሮ አንዳንድ ምርቶችን የግድ ከውጭ ማስገባት እንደሚኖርባት በመጠቆምም፣ የቀረጥ ውሳኔው ደግሞ አሜሪካዊያን ሸማቾችን የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡

የትራምፕ ሀሳብ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የአሜሪካን ኢኮኖሚ እናሳድጋለን ከሚል አመክንዮ የመጣ ነው ያሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ ይህ ግን አሁን ላይ ጭምር የአሜሪካንን “ስቶክ ማርኬት” እየጎዳው እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...