‘የትዝታዬ ማሕደር’ ሚያዝያ 5 2017 ዓ.ም ይመረቃል

Date:

“ዳግላስ ጴጥሮስ “በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀው፣ በርካታ መፅሀፎችን እና መጣጥፎችን ያስነበበው ደራሲ ጌታቸው በለጠ ‘የትዝታዬ ማሕደር’ በሚል ርዕስ የሕይወት ታሪኩን  ፅፎ በቅርቡ ያስመርቃል፡፡

ደራሲ ጌታቸው  በለጠ፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለ ሲሆን በየጊዜው በሚሰጣቸው የማህበራዊ እና የኪነ ጥበባት ሂሶችም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ሚድያዎች ላይ በመቅረብ ቃለ- መጠይቆች በመስጠት ከበሬታን ያገኘ ደራሲ ነው።
ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  በጋዜጦች ላይ በመፃፍ አቅሙን ያሳየ የብዕር ሰው ነው።

ደራሲ ጌታቸው በለጠ የሚያስመርቀው መፅሀፍ፣448 ገፆች ያሉት ሲሆን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ያሳለፈውን ሕይወት በመፅሀፉ ላይ አካቷል፡፡

የደራሲ ጌታቸው መፅሀፍ 1000ብር የሚሸጥ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ታዋቂ ደራሲያን፣ እና የቅርብ ወዳጆቹ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...