የኖቤል ኮሚቴ ከሰላም በላይ ፖለቲካን እንደሚያስቀድም አሳይቷል

Date:

የኋይት ሃውስ ቃለ አቀባይ ስቴቨን ቼኡንግ ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አለማሸነፋቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሚቴው ከሰላም በላይ ፖለቲካን ማስበለጡን አሳይቷል ብለዋል።

ቃለ አቀባዩ ” ትራምፕ የሰብዓዊነት ማዕከል ናቸው” በማለት ሌሎች ሊሞክሩ የማይደፍሩትን ነገር አሳክተዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ትራምፕ በተደጋጋሚ ላቆምኳቸው ጦርነቶች የሰላም ሽልማት አልተሰጠኝም ሲሉ ዘንድሮ በተለይ የእስራኤል እና ኢራንን ጦርነት በማስቆም እንደዚሁም ደግሞ ከሰሞኑ በጋዛ ለተፈፀመው የሰላም ስምምነት በነበራቸው ሚና ሽልማቱን ይገባኛል ሲሉ በተደጋጋሚ በግልጽ ተናግረው ነበር።

ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ያልተዋጉትን ጦርነት ጨምሮ የሰርቢያና ኮሶቮ፣ የአርሜኒያ እና አዘርባጃን እንደዚሁም የህንድ እና ፓኪስታንን ግጭቶች አስቁሜያለሁ ብለው መናገራቸው ይታወሳል።

ዘገባው የአልጄዚራ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...