የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ ጀመረ

Date:

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች ፤የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም አመልካች በኦንላይን በማመልከት በቀጠሮ ቀን  ብቻ ወደ ተቋሙ መሄድ እና  መስተናገድ እንደሚቻል አሳውቋል።

በኦን ላይን መሙላት ያልቻሉ አስቸኳይ ጉዳይ ያላቸው አመልካቾች በአካል መጥተው መስተናገድ እንደሚችሉም ገልጿል።

በተጨማሪ አገልግሎቱ ” ከግንቦት 6/ 2017 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ከጠዋቱ 12:00 – 8:00 ሰአት ድረስ የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት ደግሞ ከ9:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰአት በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ አስታውቆ፤ተገልጋዮች በቀጠሯቸው ቀን ብቻ ወደ ተቋሙ  በመምጣት ተስተናገዱ   ብሏል።

ከቀጠሮ ቀን ውጭ በተቋሙ አካባቢ መቆምም ሆነ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲልም አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...