በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በደረሰው ከፍተኛ ንፋስና በረዶ የቀላቀለበት ከባድ ዝናብ፣ በአካባቢው በሚገኙ የአበባና የፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡
በዚህም ከትናንት በስቲያ ሰኞ ሁለት ዋና ዋና እርሻዎች ላይ የሚገኙት ግሪን ሐውሶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ካፒታል ዘግቧል፡፡
ከእነዚህ ሁለት እርሻዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች ስምንት የሚሆኑ እርሻዎችም ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል ።
በደረሰው አደጋ ምክንያት በአካባቢው የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የእርሻ ስራዎችን ይበልጥ ተፅዕኖ ዉስጥ እንደሚጥለው ተገልጿል።
በአደጋው የተጎዱት አምራቾች፣ በቀጣይ ወራት ዉስጥ ወደ ስራ ካልተመለሱ በባንክ ያለባቸው ብድርና ለመንግሥት የሚከፍሉት ግብር ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድርባቸው መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡
