የአቡ ዳቢ የዩክሬን ድርድር ባልተቋጩ የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር

Date:

​ስፑትኒክ ያገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​▪️ የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን በአቡ ዳቢ ከአሜሪካ ጋር በተደረገው የሦስትዮሽ ውይይት ከዚህ በፊት በተለየ ቀጥተኛ ግንኙነት አድርገዋል።

​▪️ ለሁለት ቀናት የቆየው ድርድር “በገንቢ እና አዎንታዊ መንፈስ” ተካሂዷል።

​▪️ ውይይቶቹ ትኩረታቸውን ያደረጉት አሜሪካ ባቀረበችው የሰላም ማዕቀፍ እልባት ባላገኙ ነጥቦች ላይ እና ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚያግዙ የጋራ መተማመኛ እርምጃዎች ላይ ነው።

​▪️ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግጭቶች ያለ ውይይት ሊፈቱ እንደማይችሉ አጽንኦት በመስጠት ለዓለም አቀፍ የግጭት አፈታት ጥረቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ቃል ገብታለች።

​▪️ዶናልድ ትራምፕ ድርድሩ እንዲመቻች ላደረጉት ሚና አድናቆቷን ገልጻለች።

👉 ስብሰባዎቹ አዲስ በተቋቋመው የሩሲያ-አሜሪካ-ዩክሬን የሦስትዮሽ የደህንነት ጉዳዮች የሥራ ቡድን የተካሄው የመጀመሪያው ነው። ቡድኑ በአድሚራል ኢጎር ኮስቲዩኮቭ የሚመሩ ከፍተኛ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን አካቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...