ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በወልቂጤ ከተማ የሚገነባው የአትሌት ሰለሞን ባረጋ ሎጅ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የሎጁ ግንባታ ቀደም ሲል አትሌት ሰለሞን ባረጋ በሽልማት በተበረከተለት 15 ሺህ ካሬ ቦታ ላይ ነው።
ግንባታው 300 ሚሊዮን የሚፈጅ ሲሆን ደረጃውም ባለ አምስት ኮከብ ሎጅ እንደሆነ ተገልጿል።
እንደ ወልቂጤ ኤፍ ኤም ዘገባ የሎጁ ግንባታ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።
