የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የቱርኩን ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሊያመጣ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) በቱርክ አገር በጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርት ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈውን ኬ-ኤስ-ኤስ ኩባንያን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የኩባንያው አመራሮች በኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፣ በተለይም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ለማምረት ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ኬ-ኤስ-ኤስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት የሚያስችለውን የንግድ ማመቻቸትና ድጋፍ ከአዲስ ንግድ ምክር ቤት ጠይቋል።

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ዘሃራ መሐመድ በበኩላቸው፣ ምክር ቤቱ ይህን ዓለም አቀፍ ባለሀብት በጽኑ እንደሚደግፍና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በማገናኘት ወደ ሥራ እንዲገባ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ይህ የተገለፀዉ በምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የተመራ ከፍተኛ የንግድ ልዑክ በኢስታንቡል የሚገኘውን የኩባንያውን ዋና መሥሪያ ቤት በመጎብኘት በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት ዕድል ሰፊ ገለጻ ባደረገበት ወቅት ነዉ።

እ.አ.አ በ2009 በመሐመድ ሳፓኖግሉ የተመሠረተው ኬ-ኤስ-ኤስ፣ በአሁኑ ወቅት ምርቶቹን ከ80 በላይ ለሚሆኑ አገራት (በተለይም ለሩሲያ፣ ለመካከለኛው ምስራቅና ለሰሜን አፍሪካ) እንደሚልክ መረጃዎች ያመለክታሉ። ኩባንያው ከአልባሳት ምርት በተጨማሪ በሎጂስቲክስ መፍትሔዎችም የታወቀና በዘርፉ ታማኝነትን ያተረፈ ብራንድ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...