የዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን ከ125  ሐገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ አልተካተተችም

Date:

ስታርትአፕ ብሊንክ (StartupBlink) የተሰኘው የጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው የ2026 የዓለም አቀፍ የጅማሮ (ስታርትአፕ) ኢኮ-ሲስተም መረጃ መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ አህጉር ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ 61ኛ ሆና ተመዝግባለች።

ተቋሙ ከ125 በላይ ሀገራትን የገመገመ ሲሆን፣ ለደረጃው መመዘኛ አድርጎ የተጠቀመው የሕግ ማዕቀፍ፣ የካፒታል አቅርቦት፣ የግብር ሥርዓት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና ዓለም አቀፍ ተንቀሳቃሽነትን መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።

በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ መሠረት ኬንያ በ48 ነጥብ ከዓለም 68ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃን ሆናለች፣ ኬፕ ቨርዴ በ47 ነጥብ ከዓለም 70ኛ በመሆን ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በተጨማሪም ሞሮኮ 80ኛ፣ ኮት ዲቯር 81ኛ፣ ናሚቢያ 83ኛ፣ ቱኒዝያ 87ኛ፣ ሩዋንዳ 91ኛ፣ ግብፅ 94ኛ እና ናይጄሪያ 95ኛ በመያዝ ከአፍሪካ 10 ቀዳሚ የኢኖቬሽን ሥነ-ምሕዳር ያላቸው ሀገራት ተርታ ተቀምጠዋል።

ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋም ይፋ ባደረገው የ2026 የዓለም አቀፍ የጅማሮ (ስታርትአፕ) ኢኮ-ሲስተም ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በዓለም ቀዳሚ ከሆኑ 125 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች።

ተቋሙ ደረጃውን ያወጣው ሀገራቱ ያላቸውን የሕግ ማዕቀፍ፣ የካፒታል አቅርቦት፣ የግብር ሥርዓት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና ዓለም አቀፍ ተንቀሳቃሽነትን መሠረት በማድረግ ነው ተብሏል።

የጎረቤት ሀገራት ወደ ዝርዝሩ ሊገቡ የቻሉት የተሳለጠ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በመዘርጋታቸው እና ለጅማሮ ሥራዎች አመቺ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎችን በማፅደቃቸው እንደሆነ ሪፖርቱ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተተችው በካፒታል አቅርቦት እና በዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ላይ ባሉ ውስብስብ አሠራሮች ምክንያት እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው፣ ሀገራት በደረጃ ሰንጠረዡ ውስጥ ከፍ እንዲሉ ያደረጋቸው ዋናው ምክንያት የውጭ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ ግልጽ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ መቻላቸው ነው።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በመተግበር ላይ ብትሆንም፣ በሪፖርቱ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ለማሟላት በተለይም የውጭ ካፒታልን በነፃነት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማውጣት የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎች ላይ ገና ብዙ ሥራዎች እንደሚቀሩ ይገመታል።

በጉዳዩ ላይ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ ባይኖርም፣ መንግሥት የስታርትአፕ አዋጅን ለማፅደቅና የኢንቨስትመንት ከባቢውን ለማሻሻል ጥረት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

(አሐዱ ራድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...