የአዲስ አበባን መለያ የተነቀሰችው ዝነኛ ተዋናይ

Date:

እውቋ የሆሊውድ ተዋናይት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎቿ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ የሰውነት ንቅሳቷ ከማጌጫነት ያለፈ ነው።

አንጀሊና በሰውነቷ ላይ ንቅሳት ማድረግ የጀመረችው ከዓመታት በፊት ሲሆን፣ ወሳኝ የምትላቸውን ጉዳዮችን በንቅሳት መልክ በሰውነቷ ላይ ታሰፍራለች።

አንጀሊና ጆሊ ከተነቀሰቻቸው ምልክቶች መካከል በቀኝ ክንዷ ላይ የከተሞች መለያ ኮድ ይገኛል። ይህ “N 9° 2′ 0″ E 38° 45′ 0″ የሚለው ንቅሳት የዚህ ንቅሳት ትርጉም የጂፒኤስ መለያ ነው።

ይህም በጉዲፈቻ የወሰደቻት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችውን አንደኛ ልጇን ዘሀራን ለማስታወስ ስትል የተነቀሰችው ነው።

ቁጥሩ የአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መለያ ኮድ ሲሆን፤ በሌላ አገላለጽ ይህንን ቁጥር ጉግል ላይ ብንፈልገው የአዲስ አበባን ካርታ ያሳያል።

አንጀሊና ጆሊ በተጨማሪም በትከሻዋ እና በክንዶቿ ላይ የተለያዩ ትርጉም ያላቸው ንቅሳቶችን አስፍራለች።

ስለ እምነት እና የመንፈስ ብርታትን በተመለከተ የተጻፉ ጥቅሶች፣ የልጆቿን የልደት ቀን እና ስም እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የወሰደቻቸው የጉዲፈቻ ልጆቿ የትውልድ ሀገር መለያ ኮድ ከንቅሳቶቿ መካከል ይገኙበታል።

በዚህም መሰረት ሜይ 13, 1940 የሚል የሮማውያን ቁጥር ያለበት ንቅሳትም ተነቅሳለች።

ይህ ቀን የሚያመለክተው በ1950 ዎቹ የእንግሊዝ  ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል እስካሁንም ዝነኛ የሆነውን አባባል የተናገሩበት ቀን ነው። ቸርችል በእለቱ ለሀገራቸው ሕዝብ ንግግር ባቀረቡበት ወቅት “ከደም፣ ከእንባ እና ከላብ ውጪ የምሰጣችሁ ነገር የለኝም” በማለት ተናግረው ነበር ።

ይህ አባባላቸው እስካሁንም ድረስ የሚጠቀስ ሲሆን፤ አንጀሊና ጆሊም ይህንን ንግግር ለማሰብ ነው ቀኑን በግራ ክንዷ ላይ የተነቀሰችው።

የአዲስ አበባን መለያ በሰውነቷ ላይ ተነቅሳ የምትዞረው ዝነኛ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ፣ አዲስ አበባን ሰሞኑን የጎበኘች ሲሆን፤ ብሔራዊ ቤተመንግስት ተገኝታ ጉብኝት አድርጋለች ።

EBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...