የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሦስቱ ሀገራት የትራንስፖርት ኮሪደር 214.47 ሚሊዮን ዶላር አፀደቀ

Date:

የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን በሦስቱ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን፣ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እንደሚያሳድግ የሚጠበቀው የክልላዊ ውህደት መሪ ፕሮጀክት የሆነውን የደቡብ ሱዳን – ኢትዮጵያ – ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍን ለማስጀመር 214.47 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጽድቋል።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ በሦስቱ አገሮች መካከል የንግድ ልውውጥን፣ ግንኙነትን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማሳደግ ታስቦ ነው።

የገንዘብ ድጋፉ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተቀነሰ የወለድ መጠን የተገኘ ሲሆን ለኢትዮጵያ 181.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለጅቡቲ 29.71 ሚሊዮን ዶላር እና ለደቡብ ሱዳን 1.96 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የእርዳታ ድጎማዎችን ያካትታል።

በፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ በኢትዮጵያ፣ የ67 ኪሎ ሜትር ፈጣን መንገድ ግንባታን እና የትራፊክ አስተዳደርን የሚያሻሽሉ ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓቶች መዘርጋትን እንደሚደግፍ ተገልጿል።

እንዲሁም ለገጠር ማህበረሰቦች ተደራሽነትን ለማሳደግ 50 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የአካባቢ መንገዶችን ያሻሽላል ተብሏል።

በተጨማሪም በጅቡቲ 18 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ዲኪል-ሙሉድ የተባለውን የመንገድ ክፍል ለማሻሻል እና ደቡብ ሱዳን ደግሞ 280 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ካፖኤታ-ቦማ-ራአድ መንገድ ለማሻሻል የሚያስችሉ የቴክኒክ ጥናቶችን ለማዘመን እንደሚያገለግል ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...