አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ ውሳኔ ተላለፈባቸው

Date:

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በሰባት ዓመት ከሁለት ወር ጽኑ እስራት እና በአምስት ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ጠበቃቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

የአቶ ታዬ ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ እንደተናገሩት፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ታኅሣሥ 05 ቀን 2025 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈባቸው ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ በተባሉበት “ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት” በሚለው ክስ ነው።

ጠበቃው፣ 13 የቅጣት ማቅለያ ነጥቦችን አቅርበን ፍርድ ቤቱ ከእነዚህ ውስጥ 12ቱን ተቀብሏል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ዛሬ የተሰጠው የቅጣት ውሳኔም የቅጣት የማቅለያ ክርክሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። የዐቃቤ ሕግ ቅጣቱ እንዲጨምር ያቀረበው ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል ብለዋል ጠበቃው።

አቶ አበራ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ለማለት ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ውሳኔው “ሁሉንም የመከላከያ ምስክሮች ሳይሰማ” የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ፤ ከተዘረዘሩት አምስት የመከላከያ ምስክሮች ውስጥ የተሰሙት ሁለቱ ብቻ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

ጠበቃው አክለውም፣ ዋና ምስክሮች የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የመከላከያ ምስክሮች ተብለው ቢዘረዘሩም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ገልጸዋል።

እነዚህን ምስክሮች አለመስማት ተከሳሹ ራሱን ሙሉ በሙሉ የመከላከል ሕገ መንግሥታዊ መብቱን የነፈገ ነው ያሉት አቶ አበራ፣ በይግባኝ ሂደቱ ቅጣቱን መቃወማቸውን እንደሚቀጥሉ አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...