የኢሕአፓ ዋና ጸኃፊ የመንግስት ሚዲያዎችን አምርረው ወቀሱ

Date:


የኢሕአፓ ዋና ጸኃፊ ሚስጥረሥላሴ ታምራት፣ በወቅታዊው የምርጫ ክርክር ሂደት ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ገለልተኝነት የጎደለው አሠራር እያሳዩ መሆኑን በብርቱ ተችተዋል።

እንደ ዋና ጸኃፊዋ ገለጻ፣ ሚዲያዎቹ ክርክሩን የሚያካሂዱባቸውን ቦታዎች የሚመርጡት ሆን ተብሎ የብልጽግና ፓርቲን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ለማስተዋወቅና ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያመች ታስቦ ነው።

ሚስጥረሥላሴ በኢቢሲ በተዘጋጀው የክርክር መድረክ ላይ ፓርቲያቸውን ወክለው በተሳተፉበት ወቅት፣ ክርክሩን የመራው ባለሙያ መቶ በመቶ የገዢው ፓርቲን ስራዎች ሲያስተዋውቅ እንደነበር ታዝበዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎች የቦታ መረጣ እና አቀራረብ (Framing) ያላቸውን ተፅዕኖ እያወቁ፣ ሆን ብለው ለገዢው ፓርቲ አድልዎ ማድረጋቸው ተቋማቱ ራሳቸውን እንደ “ተጨማሪ የብልጽግና ወኪል” እንዲቆጥሩ አድርጓቸዋል ሲሉ ወቅሰዋል።

ዋና ጸኃፊዋ አክለውም፣ ሚዲያዎቹ ተቃውሞ ያለባቸውንና የሚዲያዎቹን ወገንተኝነት የነቀፉባቸውን የንግግር ክፍሎች ቆርጠው እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

በተለይም አዲስ ቲቪ በምርጫ እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን ሙሉ ቃለ-መጠይቅ አፍኖ ማስቀሩን በመጥቀስ፣ የሕዝብ ሚዲያ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መሆን እንደሌለበትና በምርጫ ወቅት እንኳን ገለልተኝነት ሊታይ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢሕአፓ በምርጫው ሂደት እስከመጨረሻው ለመቀጠል ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የሚዲያ ነፃነትና የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት መሆኑን ሚስጥረሥላሴ አስታውሰዋል።

በዚህ ረገድ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባለሙያዎች ያሳዩትን ሙያዊ ብቃት  ያደነቁ ሲሆን፣ ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች ግን ይህንን መርሕ በግልጽ መጣሳቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...