የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች ማህበር ተመሠረተ

Date:

ማህበሩ በዋናነት የይዘት ፈጣሪዎች እንቅስቃሴ ላይ በማተኮር ይሰራል ተብሏል፡፡

ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ ይዘት ፈጣሪዎች በአካውንቶቻቸው ላይ እስከ ማጥፋት የደረሰ እገዳ እና እይታ መቀነስን የተመለከቱ ጉዳዮች መፍትሔ  ማስጠት ፣ያለአግባብ በአካውንቶቻቸው ላይ የሚወሰድ  እርምጃዎችን ከሚመለከታቸው የማህበራዊ ሚዲያው ዘርፍ  ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመጣመር መስራት ከማህበሩ አላማዎች መሀከል ዋናው ነው  ተብሏል፡፡

በተጨማሪም  ማህበሩ ለይዘት ፈጣሪዎች ጥበቃ ማድረግ፣የቀረፃ ነፃነት መስጠት፣የማህበራዊ ሚዲያ እውቀትን ማስፋት፣የሀገርን ገፅታ የሚገነቡ ስራዎች  ላይ እንዲሰሩ ማበረታታት የማህበሩ አላማዎች ናቸው ተብለዋል።

ማህበሩ በ18 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አማካኝነት ስራውን መጀመሩም ተነግሯል።

ማንኛውም እድሜያቸው ከ 18 አመት በላይ የሆኑ  ግለሰቦች እና ተቋማት ጭምር  በማህበሩ ስር መካተት ይችላሉ ያለው  ማህበሩ፥ እነዚህ ይዘት ፈጣዎች ታዲያ  ቢያንስ ከ  5 ሺህ  በላይ ተከታይ ሊኖራቸው ይገባል ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...