የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሠራተኞች፤ አመራርና ተገበያዮች 129ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከበሩ

Date:

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የምርት ገበያው አመራሮች፣ ሠራተኞችና ተገበያዮች በተገኙበት የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በምርት ገበያው ዋና መሥሪያ ቤት ተከበሯል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ አቶ መርጊያ ባይሣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት ያስተላለፉ ሲኾን አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ነፃነትና ክብር ያላት ሀገር በመረከባችን ዕድለኞች ነን፣ ለዚህ ክብር ያበቁን ጀግኖች አባቶቻችን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

አድዋ የጥቁር ህዝቦች የነጻነትና የጀግንነት መገለጫ ነው፡፡  የዚህ ዘመን ትውልድ የአባቶቻችንን አደራ በመረከብና ዘመኑ የሚጠይቀውን ጀግንነት በመፈፀም ሀገራችን ወደ ብልፅግና ለመሻገር የሚደርገውን ጥረት በባለቤትነት የማሳካት አደራ አለበት ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው የምርት ገበያው አመራሮች፣ ሠራተኞችና ተገበያዮች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ በታማኝነትና በትጋት በማገልገል የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነቸውን ሀገራችን ኢትዮጵያን  የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት ከምን ጊዜውም በላይ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለክብረ በዓሉን  የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቶ ዳዊት ሙራ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቅርበገው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...