የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኢንስቲትዩት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ሊጀምር ነው

Date:

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኢንስቲትዩት የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቀብሎ ማሰልጠን ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኢንስቲትዩት በቴክኒክና ሙያ ደረጃ ተማሪዎችን ለማሰልጠን እየሰራ ይገኛል።

በ2018 ዓ.ም በደረጃ አንድ፣ ሁለትና ሶስት ተማሪዎችን ለማስተማር ፍቃድ አግኝቷል፤ በዚህም 12ኛ ክፍል ማለፍ የቻሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር ተናግረዋል።

በቀጣይም በቢሾፍቱ 62 ሄክታር መሬት ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረው፤ ማዕከሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ የተቋሙን አቅምና የተማረ የሰው ኃይል ቁጥር እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ የባቡር ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት ኢንጂነር ህሊና፤ ነገር ግን የዘርፉ ዕድገት እንደተጠበቀው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...