ህንድና ፓኪስታን ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንዲሰሩ አሜሪካ አሳሰበች

Date:

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደገለጹት አሜሪካ በህንድና ፓኪስታን መሃል የተፈጠረውን ግጭት በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ከሁለቱ ሃገራ መሪዎች ጋር የአሜሪካ ባለስልጣናት ውይይት ማድረጋውን ገልጸው ሃገራቱ በደቡብ እስያ የረጅም ጊዜ ሰላምና ቀጠናዊ መረጋጋትን የሚያስጠብቅ ሃላፊነት የተሞላበት መፍትሄ ለማምጣት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ከአሜሪካ በተጨማሪም ሩሲያ ጃፓንና ጀርመን ሁለቱ ሃገራት ግጭቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ህንድና ፓኪስታን ወደ ግጭት እንዲገቡ ዋና ምክኒያት የሆናቸው የካሽሚር ግዛት ከ1947 ጀምሮ በሁለቱም ወገኖች የይገባኛል ጥያቄ ሲነሳበት የቆየ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡

ሁለቱ ሃገራት ከብሪታኒያ ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጡ ቦሃላ በግዛቱ የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ተደጋጋሚ ጦርነቶችን አድርገው የሚያውቁ ሲሆን 1965 ላይ በምድርና ባየር የታገዘ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...