በኬንያ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ደመቀ አጥናፉን ምንጭ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. የአፍሪካ መሪዎች እና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃልደ
ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ እንደሆነ የተነገረለት ሕዳሴ ግድብ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው ሲካሄድ ቆይቷል።
አምባሳደር ደመቀ እንደተናገሩት የሕዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. በይፋ ይካሄዳል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ከአስር ዓመታት በላይ ፈጅቶ የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ በይፋ እንደሚመረቅ ማስታወቁ ይታወቃል።
