የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአርሲ ሺርካ ለደረሰው ጥቃት መግለጫ አወጣ

Date:

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሺርካ ወረዳ በንፁሐን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጥቃት አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡ *’ምክር ቤቱ በንፁሐን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል። * ድርጊቱ የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል፣ ይልቁኑም በሃይማኖቶች መካከል ለዘመናት የኖረውን የመከባበር እሴት በመናድ፣ በአማኞች መካከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር የተቀነባበረ እኩይ ሴራ መሆኑን ምክር ቤቱ አምኗል።

መንግስት አጥፊዎቹን በአፋጣኝ ለይቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ምክር ቤቱ በጥብቅ ጠይቋል። ለሟች ቤተሰቦች ፈጣሪ (አላህ) መፅናናቱን እንዲሰጥ ምክር ቤቱ ምኞቱን ገልጿል። Via የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው

ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሆነ ፎርቹን ጋዜጣ...

የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ ፣ ሀገር አቀፍ ሚሊሻ ይደራጅ የሚሉ አጀንዳዎች ቀርበዋል

በፌደራል ከተሞች ጉዳይ ጥላ ውስጥ የወደቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤...

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያው የአይን ሐኪም ዶክተር ጳውሎስ አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን...

ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ወጡ

በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኢትዮ...