የኢትዮጵያና ሶማሊያ የወደብ ቴክኒክ ኮሚቴ ስራ ማቆሙን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘግቧል።
በቱርክ አሸማጋይነት ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሲያደርጉት የነበረው የወደብ የቴክኒክ ኮሚቴ ስራ ለጊዜው መቋረጡ ታውቋል።
አንካራ ባለፈው አመት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግስታትን ወደ ጠረጴዛ ካቀረበች በኋላ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ወደብ ለማገናኘት የሚያስችል የቴክኒክ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ያለው አፍሪካንስ ኢንተሌጀንስ ውይይቶቹ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጠዋል ብሏል።
