የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጎረቤቶቿን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት እንድታከብር ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠየቁ

Date:

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳለህ፣ ኢትዮጵያ የተሳሳተና ጊዜው ያለፈበት በኃይል ወይም በዲፕሎማሲዊ መንገድ የባሕር ኃይል የማቋቋም ወይም የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ኤርትራን እያስገረማት እንደኾነ ለዲፕሎማቶች በሠጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።

ኦስማን፣ ኢትዮጵያ የጎረቤቶቿን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት እንድታከብር ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የኤርትራ ጦር ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል የሚሉ አካላት፣ ለኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግር ኤርትራን ተጠያቂ ማድረግ የሚፈልጉ ናቸው በማለትም ኦስማን ከሰዋል።

ኦስማን፣ በሕወሓትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ባለው ሽኩቻ ውስጥ ኤርትራ ሚና አላት የሚለውን ውንጀላም አስተባብለዋል።

Via ዋዜማ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...