የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የጨፌ ስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ሹመትን አጽድቋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በሥራ ላይ ባዋለው አዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በክልሉ ስድስት አዳዲስ ዞኖች አዋቅሯል።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት የሚመሩ አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ በጨፌ ኦሮሚያ ሹመት ሰጥቷል።
በዚህ መዋቅራዊ ሽግግር መሠረት አዲሶቹ ዞኖች ያቀፏቸው አካባቢዎች፦
ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ምስራቅ እና ምዕራብ ሀርጌ ዞኖችን አካትቷል ።
ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ደግሞ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ የአሰላ ከተማ እና የዶዶላ ከተማን አቀፎ ተደራጅቷል።
ደቡብ ኦሮሚያ ዞን ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቡሌ ሆራ ከተማ፣ ሞያሌ ከተማ እና የሻኪሶ ከተማን አካቷል ።
ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በበኩሉ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባ ቦር፣ ጅማ፣ የአጋሮ ከተማ እና የመቱ ከተማን ይዞ ተዋቅሯል።
ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና የነጆ ከተማን ይዞ ተዋቅሯል ።
የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ደግሞ ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም የአምቦ፣ የባቱ፣ የሆለታ፣ የሞጆ፣ የሰንዳፋ በኬ፣ የሸኖ እና የወሊሶ ከተማዎችን አካቶ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት የሚመሩት ፦
• አቶ አብዱርራህማን አብደላ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ መስፍን መላኩ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር ረሻድ ከማል፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር መንግሥቱ በቀለ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ኢድሪስ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ሀጂ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
ይህ የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ አዲስ በጸደቀው አዋጅ 267/2019 መሰረት ያደረገ ነው፡፡
7. ዶ/ር ቶላ በሪሶ -የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ
8. አቶ ጉዮ ዋሪዮ- የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
9. ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ- የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
10. አቶ ተስፋዬ ቱሉ- የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
11. ዶ/ር አብዲ ዩያ- የእቅድና ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. ድ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
13. ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ- የጤና ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ተሾመ ቦጋለ-የግብርና ቢሮ ኃላፊ
15. ዶ/ር ነመራ ገበየሁ- የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ ታረቀኝ ቡልልታ- የኢንተርፕራይዝና አንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር አደሬ አሰፋ- የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
18. ወ/ሮ መሰረት አሰፋ- የመሬት ቢሮ ኃላፊ
19. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን- የሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ
20. አቶ ጥላሁን ወርቁ- የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ
21. ዶ/ር አያንቱ ጉተታ- የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
22. ወ/ሮ እልዳና ሱሌማን- የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
23. አቶ ቲጃኒ ናስር- የሰላም ቢሮ ኃላፊ
24. ወ/ሮ ሮዛ ቢያ- የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ- የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ
26. ኢንጂነር ሃቢብ ቁምቢ- የመንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ
27. ኢንጂነር ማሪያ ጉታ- የውሃ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሹመዋል፡፡
