የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ህብረተሰቡ ፈቃድ በሌላቸው የቤት ልማት ፕሮጀክቶች እንዳይታለል ማሳሰቢያ ሰጠ

Date:

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማህበራዊ ሚዲያ ቤት ግዙ በማለት ፈቃድ ሳይኖራቸው ገንዘብ ከሚሰበስቡ ህገ ወጥ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ባለስልጣኑ ለአሐዱ እንዳስታወቀው ፈቃድ ያልተሰጣቸው አንዳንድ የቤት ፕሮጀክቶች በተለይም በሊንክ እና በቴሌግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ያስተዋውቃሉ ብሏል።

እነዚህ አካላት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በማስመሰል ከህብረተሰቡ ገንዘብ እየሰበሰቡ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የምርመራ እና አፈጻጸም ክፍል ሃላፊ ወይዘሮ ህሊና ስንታየሁ የሰነደ መዋለ ንዋዮችን በሚመለከት የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ላይ በየጊዜው ክትትል እንደሚደረግ ገልጸው በዚህም በማህበራዊ ሚዲያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላት መኖራቸውንና በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን፣ ውጤቱንም ወደፊት እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ህጋዊ ፈቃድ በሌላቸው አካላት ፕሮጀክቶች ላይ ሀብቱን ኢንቨስት ከማድረግ እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ የሰጡት ወይዘሮ ህሊና ማንኛውንም የኢንቨስትመንት ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት የፕሮጀክቶቹን ህጋዊነት ከባለስልጣኑ ማረጋገጥ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በ2013 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1248 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠር ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አክሲዮን እንመሰርታለን በሚል ሽፋን በህገወጥ መንገድ ከህብረተሰቡ ገንዘብ የሚሰበስቡ አካላት መኖራቸውን አስታውሶ ህብረተሰቡ ህጋዊ እውቅና ለሌላቸው አካላት ገንዘቡን ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ እና በድርጊቱ በሚሳተፉ አካላት ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...