በመድረኩ የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የአለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ የህዝብ ቁጥራቸው ብዙ እና በርካታ ስደተኞች ተቀባይ በሆኑ ሀገራት የምግብ ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ እንደሆነ ተመላክቷል።
“ደህንነቱ ካልተጠበቀ ምግብ አይደለም” የሚል አቋም ያለው የአለም ምግብ ፕሮግራም በሀገራችን ኢትዮጵያ ምግብን ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ባህል መሆን አለበት ያለ ሲሆን ሳይንስን መሰረት ያደረገ ጥናቶች በስፋት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁሟል።
