የዓለም ጤና ድርጅት በ2025 የጤና ዕርዳታ እስከ 40% ሊቀንስ እንደሚችል አስጠነቀቀ

Date:

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በ2025 ዓ.ም. ለጤና ዘርፍ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ እስከ 40 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ትንበያውን ይፋ አድርጓል።

ይህ ቅነሳ በውጭ ዕርዳታ ላይ ከፍተኛ ጥገኝነት ባላቸው በርካታ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ላይ ከባድ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርና ዜጎች ለጤና አገልግሎት ከራሳቸው ኪስ የሚያወጡት ወጪ በእጅጉ እንዲጨምር እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ከሁለት ሳምንት በፊት በእስያ ልማት ባንክ በተዘጋጀው ኢንስፓየር ፎረም ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ባቀረበው ግምት መሠረት ነው።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ለጤና የሚውለው ኦፊሴላዊ የልማት እርዳታ (ODA) በ2025 ከ2023 ደረጃ ጋር ሲነፃፀር ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወደ 15 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ሊቀንስ ይችላል።

ይህ አኃዝ እኤአ በ2015 ዓ.ም. ከነበረው 18 ቢሊዮን ዶላር የጤና ኦዲኤ ፈንድ በታች በመሆን፣ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሏል።

የዚህ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ ዋነኛ ምክንያት፣ ለዓለም አቀፍ ጤና ዕርዳታ ከሚሰጡ ትልልቅ ለጋሽ አገሮች መካከል፣ እንደ አሜሪካ እና ሌሎች በርካታ አገሮች የገንዘብ ድጋፋቸውን በእጅጉ መቀነሳቸው እንደሆነ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...