የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በራሺያ ላይ 40 የጦር አውሮፕላኖችን አወደሙ

Date:

ዩክሬን በ40 የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ላይ በአራት ወታደራዊ ካምፖች ላይ ተከታታይ ከባድ ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ጦርነት ትልቁን የረዥም ርቀት ጥቃት እሁድ እለት ማጠናቀቋን ገልጻለች።

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት 117 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኤስቢዩ የደህንነት አገልግሎት “የሸረሪት ድር” እየተባለ በሚጠራው ተግባር ላይ “34 በመቶ የሩሲያ ስትራቴጂካዊ የክሩዝ ሚሳይል ተሸካሚዎችን” መቷል ብለዋል። የዩክሬኑ ደህንነት ኤስቢዩ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጥቃቱን ሂደት ለማደራጀት አንድ ዓመት ተኩል ፈጅቷል ሲሉ ተደምጠዋል። ሩሲያ በአምስት ክልሎች የተፈፀመባትን የዩክሬን ጥቃቶችን “የሽብርተኝነት ድርጊት” በማለት ጠርታለች።

ጥቃቱ የደረሰው የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ዛሬ ሰኞ ለሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ወደ ኢስታንቡል ቱርክ በሚያቀኑበት ወቅት ነው።ውይይቱ በሲራጋን ቤተ መንግስት እንደሚጀመር ይጠበቃል። ጦርነቱን እንዴት ማቆም እንደሚቻል ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በጣም የተራራቁ በመሆናቸው የሚጠበቀውም ውጤት ዝቅተኛ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ባለስልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ በግዛታቸው ላይ ግዙፍ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል። በካርኪፍ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የሰባት አመት ህፃንን ጨምሮ ቢያንስ 6 ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተናግረዋል። በሌላ ቦታ የሩስያ መንግስት የዜና ወኪል ሪያ የሀገሪቱ የጸጥታ አገልግሎት በምስራቅ ሩሲያ የተፈፀመውን የጥቃት ሙከራ ማክሸፉን ገልጿል።

በፕሪሞርዬ ክልል ሁለት ነዋሪዎች በዩክሬን ትእዛዝ የባቡር ሀዲዱን ለማበላሸት እየሞከሩ ነበር ብሏል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ በሙሉ ወረራ ጀምረዋል። ሞስኮ በአሁኑ ጊዜ በ 2014 የጠቀለለቻትን ደቡባዊ ክራይሚያ ልሳነ ምድርን ጨምሮ 20 በመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት በእጇ ይገኛል።

የኤስቢዩ ምንጮች እንደተናገሩት ከተመቱት የሩሲያ አውሮፕላኖች መካከል ቱ-95 እና ቱ-22ኤም 3 የሚባሉ ስልታዊ የኒውክሌር አቅም ያላቸው ቦምቦች እንዲሁም ኤ-50 የቅድመ ማስጠንቀቂያ የጦር አውሮፕላኖች ይገኙበታል። አጠቃላይ ስራውን “እጅግ የተወሳሰበ ነበረ” ሲሉ ገልጸውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...