በተለያዩ የባህል የሙዚቃ ስራዎቿ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ድምፃዊት ባንቺአምላክ በላይነህ(ናርጊ) 3ኛ አልበሟን ‘እልል’ በሚል ስያሜ ምርጥና አዲስ የባህል አልበም በአንጋፋው አምባሰል ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ለአድማጭ ተመልካች አደረሰች።
“እልል” የሙዚቃ አልበም ላይ በርካታ አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አልበሙም የኢትዮጵያን ታሪክ፣ወግ፣ባህል፣ትውፊት አኗኗር፣ማህበራዊ፣ፍቅር፣ መዋደድ፣የሚዳስስ ሲሆን የሀገራችን ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች ጆሮ ገብ ዜማና የሰላ ግጥም ለአድማጭ በሚማርክ መልኩ ተቀናብረዋል።
በ”እልል”አልበም ዉስጥ ጎምላላ፥ጎንደር፥አዉደዓመት
ያሰላምሱዳን፥በልግባ፥ዉዲድ(ናርጊቁ2)አገዉኛ፥ምንጃር፥ወሎ፥ከመከሜ፥ሙዚቃዎች በተለያዬ የአዘፋፈን ስልት ተካተዋል።
ከእነዚህም ሙዚቃዎች መካከል ጎንደር፥አዉደዓመት፥ የተሰኙት የሙዚቃ ስራዎቾ ከነጭፈራዉ የቪዲዮ ክሊፕ የተሰራላቸውና በምስል ተዋህደዉ የቀረቡ ናቸዉ።ድምፃዊቷ በተለያዩ የብሔር ብሔረሰብ ሙዚቃዎች አጨዋወቷ ከመታወቋ ባሻገር ብዙዎች የሚያደንቁላት የድምፅ ቅላፄ ባለተሰጥኦ ጭምር ናት።
ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ የወሰደዉና በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጀዉ ሶስተኛዉ የባንቺአምላክ በላይነህ “እልል “አልበም የሙዚቃ አልበሙ ፕሮዱዉሰር-አንጋፋው አምባሰል ሙዚቃ በዜማ ድርሰት ሙሉጌታ አፈወርቅ ባንቺአምላክ በላይነህ የግጥም ድርሰት ሙሉጌታ አፈወርቅ አይችሉም መንግስቱ አስማማው በለዉ(ካስካሲምባዋ)የተሳተፉ ሲሆን ቀረፃ፣ ድምፅ ውህደት ማስተሪንግ ሙዚቃ ቅንብር መሐመድ ኑር ሁሴን ተጠቦበታል።
እልል አልበም 12 የሙዚቃ ዘፈኖች ያሉት ከመሆኑ በተጨማሪም በበርካቶች ተወዳጅነትን አትርፎ ዘመን መሻገር የቻለዉ ናርጊ ሙዚቃ በቁጥር 2 ተሰርቶ መቅረቡን ድምፃዊት ባንቺአምላክ በላይነህ ተናግራለች።
ላለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የሙዚቃና የጥበብ ኢንዱስትሪ ደማቅ አሻራ ማስቀመጥ የቻለዉ አንጋፋው አምባሰል ሙዚቃ ቤት በአምባሰል ሪከርድስና በአምባሰል ቲዩብ ተመልሶ በአዲስ አደረጃጀት እየመጣሲሆን”እልል”አልበምምበአምባሰል ዩቲዩብ ቻናል ተለቆ በመደመጥ ላይ የሚገኝ ነዉ።
እልል አዲስ አልበምን ለማግኘትና ሌሎች የአምባሰል ሪከርድስን የግማሽ ክፍለዘመን ጥበባዊ ስራዎችን ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት Ambassel tube
ይጎብኙ።
